"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ

የፎቶው ባለመብት, Dr. Ewa
ፓላንዳዊት ናት። አማርኛን ከ40 ዓመት በፊት ነው የተማረችው።
እሷ አማርኛ ስትማር ጓድ መንግሥቱ ምናልባት የእድገት በኅብረት ዘመቻን እያሰናዱ ነበር። እንደው የጊዜውን ርዝማኔ ለማስታወስ ነው እንጂ ነገሩ ምንም ግንኙነት የለውም።
እና ያኔ ድሮ አማርኛን በዲግሪ ተመርቃ እስከዛሬ ታስተምራለች።
ላለፉት 23 ዓመታት በርካታ ፈረንጅ በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች።
ዶ/ር ኤቫን 'አንቺ' እንበላት እንጂ በሥራዋ አንቱታን የተጎናጸፈች ሴት ናት። የአማርኛ የቁልምጫ ስሟ ሔዋን ይባላል።
ብታምኑም ባታምኑም፣እሷ የምታስተምርበት ዋርሶ ዩኒቨርስቲ አማርኛን ማስተማር ከጀመረ 75 ዓመት አልፎታል።
ለነገሩ ይሄ ምኑ ይደንቃል?
በምኒልክ ጊዜ አማርኛ በአውሮፓ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ይሰጥ ነበር

የፎቶው ባለመብት, Warsaw University- Ethiopian studies
ኔፕልስ፣ ፓሪስ እና ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲዎች አማርኛ ማስተማር ከጀመሩ 100 ዓመት አልፏቸዋል።
ይህ ለብዙ ሰው ዜና ነው።
በኔፕልስ አማርኛን ማስተማር የጀመሩት አፈወርቅ ገብረየሱስ ናቸው። ይህ ማለት በ1890ዎቹ መሆኑ ነው። ጥንት በዓድዋ ዘመን።
አማርኛ በጀርመን፣ ሐምቡርግም ዩኒቨርስቲም ይሰጣል። እዚያም ድሮ ነው የተጀመረው። ዛሬም ድረስ አለ፤ ለዚያውም ሳይቋረጥ።
ይቆጠር ከተባለ 105 ዓመት ሆኖታል፣ ዘንድሮ።
የመጀመሪያው መምህር ወልደማሪያም ደስታ የሚባሉ ሰው ናቸው። በ1909 ከአንኮበር-ሐምቡርግ ሄደው አምስት ዓመት አስተምረዋል።
በዶክተር ኤቫ አገር፣ ፖላንድ አማርኛን ማስተማር የጀመሩት ፕሮፌሰር ስቴፋን ስትሬልሲን ናቸው።የዛሬ 75 ዓመት ገደማ።
እሳቸው አማርኛን ያጠኑት በ2ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ነው። ቋንቋውን የተማሩት ደግሞ በፈረንሳይ ነው። እኚህ ሰው ከባድ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበሩ ይባላል።
በዚህም ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የወርቅ ኒሻን ተበርክቶላቸዋል።
1950ዎቹ የአፍሪካ ጥናትን ከመሠረቱ ወዲህ ብዙ ለፉ። አማርኛን በአውሮፓ አስፋፉ።
እንደ አውሮፓዊያኑ በ1981 ሕይወታቸው አለፈ።
እርሳቸው የመሠረቱት ተቋም ሰፍቶ፣ አድጎ እና ተመንድጎ በ1977 የአፍሪካ ቋንቋዎች እና ባሕል ትምህርት ክፍል ተባለ።
ከአማርኛ እና ከግዕዝ ሌላ ሐውሳ እና ስዋሂሊ ቋንቋዎችን ማስተማር ጀመረ።
ዶ/ር ኤቫ በዚህ ዘመን ባስቆጠረ ተቋም ነው አማርኛን የምታስተምረው።
እሷ ፕሮፌሰር ስቴፈንን አልደረሰችባቸውም። በዝና ነው የምታውቃቸው።
የዋርሶ ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ትምህርት ክፍል ብዙ ተማሪ አይቀበልም።
አንዱ ምክንያት ብዙ ተማሪዎች አማርኛ ከባድ ነው ብለው ስለሚፈሩ ነው። ከጀመሩት ውስጥ ሲሶዎቹ አይጨርሱትም።
በየዓመቱ በአማካይ 10 ተማሪዎችን ይቀበላል። ግዕዝን ደግሞ እንደ ኮርስ ለማንኛውም ለፈለገ ተማሪ ይሰጣል።
በ75 ዓመታት ውስጥ ቁጥራቸው ከመቶ ትንሽ ከፍ ያሉ ተማሪዎች በማስተርስ አስመርቋል። 12 የሚሆኑት ፒኤችዲ ይዘዋል።
የሆነስ ሆኖ፣ የዛሬ 40 ዓመት ኤቫ አማርኛ ለመማር እንዴት ወሰነች?

የፎቶው ባለመብት, African studies, University of Warsaw

የፎቶው ባለመብት, Dr. Gete
"አማርኛን በአጋጣሚ ነው የተማርኩት"

የፎቶው ባለመብት, Dr. Ewa
"አጋጣሚ ነው" ትላለች።
"ሒሳብ፣ ሕግ፣ ፊዚክስ እንደዚህ ዓይነት ትምህርት ብዙም አይማርከኝም ነበር። ከዚያ ይልቅ ሥነ ጥበብ፣ ኪነ ጥበብ፣ ቋንቋ እና የሩቅ አገር ባሕል ይማርከኝ ነበር።"
ዋርሶ ዩኒቨርስቲ ያኔ ድሮ የኦሪየንታል ጥናት ክፍል ነበረው። ዶ/ር ኤቫ እዚያ ስለሚሰጠው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሰማች። ተሳበች። ተመዘገበች፣ ተማረች። ተመረቀች።
ታሪኳ በአጭሩ ይኸው ነው።
አማርኛን ለአምስት ዓመታት ነው የተማረችው። አራት ዓመት በፖላንድ ከተማረች በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስኮላርሺፕ አግኝታ 1 ዓመት ወደ ኢትዮጵያ አቅንታ ከአገሬው ጋር ተምራለች።
ኢትዮጵያ የመሄድ አጋጣሚን መጀመሪያ ስታገኝ እንዴት እንደፈነደቀች።
"እኔ ወጣት በነበርኩበት በዚያ ዘመን እኛ ስለ ኢትዮጵያ ምንም አናውቅም፤ ፖላንድ ውስጥ በትምህርት ቤት ጭራሽ ስለ ኢትዮጵያ ምንም ተምረን አናውቅም. . ." ትላለች።
"አማርኛ ቋንቋ ሲሰሙት እንደ ፏፏቴ ያለ ነው"

የፎቶው ባለመብት, Dr. Ewa
አምስት ቋንቋዎችን አቀላጥፋ የምትናገረው ዶክተር ኤቫ 'ከቋንቋዎች ሁሉ አማርኛ ለምን ማረከሽ"ሕንዳዊት ታዳጊ ንጹህ ውሃ እየጠጣች " loading="lazy" width="1360" height="765" style="aspect-ratio:1360 / 765" class="bbc-139onq"/>